borkena-Ethiopian-News
  • September 3, 2022 7:17 pm

የቦርከና ድረገጽ ሁለት የአማርኛ ዜና አዘጋጆች (ጸሃፊዎችን ) አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ ስራው ከፍተኛ በሆነ የሃገር ፍቅር ስሜት እና በታማኝነት እንዲሁም ሁልጊዜም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም እና ደህንነት ግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰራ ነው፡፡

ቢሮ መግባት ሳያስፈልግ ከቤት ሆኖ ሊሰራ የሚችል ነው፡፡ ዝርዝሩ በቃለመጠየቅ ወቅት የሚገለጽ ይሆናል፡፡

ተፈላጊ ችሎታ

ትምህርት ፡ የጋዜጠኝነት ትምህርት ያለው ቢሆን ይመረጣል፡፡ ፖለቲካ ሳይንስ ፤ ታሪክ ወይንም የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በዮኒቨርሲቲ ደረጃ የተማሩ አመልካቾችም ማመልከቻቸው ግምት ውስጥ ይገባል፡፡

ልምድ ፡ ቢያንስ የስድስት ወር የጋዜጠኝነት ልምድ ያለው

የመነሻ ደመወዝ ፡ አምስት ሺህ የኢትዮጵያ ብር፡፡ ከሶስት ወር የሙከራ ቅጥር በኋላ የሚስተካከል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት ሳምንት ጊዜ ማመልከቻችሁን በ zborkena@borkena.com አድራሻ  በኢሜይል መላክ ትችላላችሁ፡፡ ከዚህ በፉት የሰራችሁን ስራ ናሙና ካለ አብሮ ማያያዝ ይቻላል፡፡

ከአክብሮት ጋር፡፡

Features:

  • የአማርኛ ዜና ማጠናቀር /መጻፍ

Location

Leave feedback about this